Support Yegna TV (የኛ ቲቪን ይደግፉ)

$100

Raised

Donation

$50,000

Goal

የኛ ቲዩብ በኦንላይን ሚዲያ በተለይ በፌስቡክ ላለፉት 8 አመታት ጠቃሚ፣ ወቅታዊ እና ታማኝ መረጃ በማቅረብ ህዝብን ሲያገለግል መቆየቱ ይታወቃል። ከየካቲት ወር 2013 ጀምሮ ደግሞ በሳተላይት ቴሌቪዥን የቤተሰብ ቴሌቪዥን ስርጭቱን የጀመረ ሲሆን የሙከራ ስርጭቱን ጨርሶ መስከረም 2014 ወደ ዋናው ስርጭቱ ገብቷል። ሆኖም ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ከፍተኛ የገንዘብ ጫና ያጋጠመን ሲሆን በተለይ ሰሞኑን አንዳንድ አካላት የዩቲዩብ ቻናላችንን ለማዘጋት የሚያደርጉትን ጥረት ስናይ ይህንን መልዕክት ለእናንተ ለቤተሰቦቻችን ለማጋራት ተገደናል፡፡ የጀመርነውን ህዝብን የማገልገል ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ አስፋፍቶ ለመቀጠል እና ያለብንን የሳተላይት ክፍያ ለመሸፈን ውድ ቤተሰቦቻችን ከጎናችን እንድትቆሙ ይህን የገቢ ማሰባሰቢያ የጀመርን ሲሆን ከታች የሚገኘውን ማስፈንጠሪያ(ሊንክ) በመጫን በገቢ ማሰባሰቢያው እንዲሳተፉ በትህትና እንጠይቃለን የኛ ቤተሰብ ይሁኑ ያትርፉ፤ ያሸንፉ! ኢትዮጵያ ያለጥርጥር ታሸንፋለች ትበለፅጋለች